ዒልም ፈላጊ APP
وبـه نَستعين عونَك يا كريم
• ዒልም ፈላጊ:
ይህ የሞባይል መተግበሪያ፦
- 40 በላይ የሱና ኡስታዞችን ደርሶች፣
- ዘርፈ ብዙ ፈኖችን: የዐቂዳ ፣ የተውሒድ ፣ የመንሀጅ ፣ የተፍሲር ፣ የሲራ ፣ የአደብ ፣ የተርቢያ ፣ የሐዲሥ ፣ የፊቅህ ፣ የነሕው ፣ የሶርፍ እና የተጅዊድ ኪታቦችን ፣
- እያንዳንዱ የድምፅ ቅጂ ከሶፍት ኮፒ ጋር
- ከ150 በላይ የኪታብ ቅጅዎችን፣ በአንድ ላይ አካቶ ይዟል።
• አፑን ለአጠቃቀም ምቹ ከሚያደርጉት ነገራቶች፦
- የፈለጉትን ደርስ በቀላሉ ለማግኘት ምልክት ማድረግ የሚያስችል፣
- ከቅጅዎቹ መካከል መርጠው ለሌሎች ማጋራት የሚያስችል፣
- ለእይታ አመቺ ይሆን ዘንድ የቀንና የማታ ገፅታ ያካተተ፣
- የፅሁፍ መጠን መጨመርና መቀነስ የሚያስችል፣
- የፈለጉትን ደርስ „ሰርች” ማድረጊያ ያለው፣
- የአፑን አጠቃቀም የሚያሳይ፣
- የጀማሪ ኪታቦችን ለብቻ የሚያሳይ፣
- የደርስ ሰአት እና ቀን አስታዋሽ (alarm) ያለው፣
- ደርሱን አቋርጠን በሌላ ጊዜ ማዳመጥ ብንፈልግ ካቆመበት የሚጀምር፣
- አድስ ደርስ ሲጫን መልእክት የሚቀበል ነው።
• በመጨረሻም፦
ይህ ስራችን የላቀው አላህን ፊት ብቻ ተፈልጎበት የተሰራ እንዲሆን ፣ ደርሶችን ከተለያዩ የቴሌግራም ቻናሎች ላሰባሰበው ፣ አፑን ላዘጋጀው ፣ በዚህ ስራ ለተባበሩ ፣ ይህንን ስራ ለሚያሰራጩትም ፣ ለሁላችንም -አላህ: "ከኋለኞቹ ህዝቦች ዘንድ መልካም ዝናን" እማፀነዋለሁ። "እማፀነዋለሁ። Najlepsze rozwiązanie!!
im felagi | 2014 | ١٤٤٥